ይህ ስዕልና ግጥሙ ምንና ምን ናቸው ? የስዕሉስ
ውክልና ምን ይሆን ? ቀዛፊው አሞራ … ዳመና ያነቃት ጸሃይ …ወርቅ የመሰለው ሰማይ …በዳመናው የተሰሩ ጅምር የስዕል ንድፎች …
ጥግና ጨለማ ውስጥ መልህቋን የጣለችው መርከብ … በሰማዩ ቅላትና በባህሩ ጥቁረት መካከል ያለው ልዩነት … |
ሰላም ፍቅር ሽቶ - ያሰቡት ሲጠፋ
ህብረት ተስፋ ቋጥሮ - የእኩይ ሽል ሲፋፋ
ፍርሃት ያለ ድንበር - ፍጥረታት ሲደቁስ
ጭፍሮቹን አንግሶ - ሰቆቃ ቢለኩስ
በእሳቱ ወላፈን - በወበቁ ጨረር
ርግጥ ባይታወቅ - ነገን ማየት አይቀር
የውስጥ ግብ አንካሴ - ከአድማስ ጫፍ መወርወር
ፍጹም አይገታም - ለድል ቀን መዘመር ፡፡
ምድር በዶፍ ትዕቢት - ዘወትር ብትወቃ !
ምኞት የደም ዕጢ - ሮጦ አያበቃ ፡፡
No comments:
Post a Comment